የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከ አልቲየሰ ጂም ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ እርምጃና ሩጫ ውድድር ለ9ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተነገረ።
በአዲሰ አበባ ወጣቶች እና ሰፓርት ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ሰፖርት ማስፋፊያ እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ እንግዳ ወርቅ ዳንኤል “ውድድሩ ወንድማማችነት ፣ መቀራረብን እና አንድነት ይፈጠራል። በተጨማሪም ማህበራዊ መሰተጋብርን ከማጠናከር ባለፈ የአካል ብቃት ባለሙያዎችን እንዲቀራረቡ ያደርጋል።” ብለዋል።
የአልቲየሰ ጂም መሰራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አሰልጣኝ ቸሩ ጉግሳ በሁለቱም ፃታ እድሜ ሳይለይ ከ5ሺህ በላይ ሰዎች በውድድሩ ይሳተፋሉ ብለዋል።
የፊታችን ዕሁድ ግንቦት 24 ከማለዳ 12 ሰአት ጀምሮ የሚካሄደው ውድድሩ መነሻውን ሰሚት አካባቢ በማድረግ ሴኤሚሲ አካባቢ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
በጃዕፈር አህመድ