የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የበኩላቸውን ሊወጡ እደሚገባ ተጠየቀ

You are currently viewing የፋይናንስ ተቋማት ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የበኩላቸውን ሊወጡ እደሚገባ ተጠየቀ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

ሀገር አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያከናወነች ላለው ስራ ድጋፍ እንዲያደርጉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስቴሩ ከፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ጋር ዛሬ ውይይት አድርጓል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እና የበጋ ስንዴ ምርት ውጤታማ ስራ ከተከናወነባቸው ዘርፎች መካከል ዋነኞቹ እንደሆኑም አንስተዋል።

የታዳሽ ኃይል የማስፋት ስራ፣ ዘላቂ መሬት አጠቃቀም እና የኮሪደር ልማት ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት እና አረንጓዴ ልማት ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየችበት እንደሆነም አመላክተዋል።

የፋይናንስ ዘርፉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ ላይ ተሳትፎ ለሚያደርጉ የፋይናንስ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

የፋይናንስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ተጋላጭ በመሆናቸው ያላቸውን ሀብትና እውቀት በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ እንዲሳተፉ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር እና ድጋፍም እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review