AMN-መስከረም 28/2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ቃለጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ነው ጉባኤውን የጀመረው፡፡

በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።