የፍትህ ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የልደታ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳትና የኮልፌ የፍትህ አካላት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀምን ጎበኙ

AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም

የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ እና የተቋም ግንባታና የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) ከተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን የልደታ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳትና የኮልፌ የፍትህ አካላት ህንፃ ግንባታ አፈፃፀምን ጎብኝተዋል።

የልደታ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳትና የግንባታ ስራው በኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን መንግስታዊ ተቋራጭ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን የፋይናሽያል አፈፃፀሙ 28 በመቶ በላይ እንዲሁም የፊዚካል አፈፃፀሙ ደግሞ ከ37 በመቶ በላይ መድረሱ ጥሩ የሚባል የስራ አፈፃፀም መሆኑን በተቋራጩና በአማካሪ ድርጅቱ በኩል ገለፃ ተደርጓል።

በተያዘለት የጊዜ ገደብ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ ተቋራጭ ድርጅቱ ከዚህ በፊት የተጠየቁ እና በቀጣይ የሚጠየቁ ክፍያዎች በወቅቱ አንዲፈፀሙለት ጠይቋል።

በተመሳሳይ የኮልፌ የፍትህ አካላት ህንፃ ግንባታ በውሉና በዲዛይኑ መሰረት ሙሉ በሙሉ አልቆ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም አጥር፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የችሎት አዳራሽ የሳውንድ ሲስተም ፣ ዴይኬር፣ የአደጋ መውጫ በሮች፣ የቪድዮ ኮንፈረንስ ክፍል እቃዎች (ፈርኒቸሮች)፣ የከርሰ ምድር ውሃ ፣ የኔትወርክ መሰረተ ልማት እና የጀነሬተር ቤት የመሳሰሉት ተጨማሪ ስራዎች ከስራዉ አስፈላጊነት እና ከበጀት አንፃር አንዴት መሰራት ይችለሉ በሚለው ዙርያ ውይይት ተደርጓል፡፡

ሚኒስትሯ የልደታ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የህንፃ ዕድሳትም ይሁን የኮልፌ የፍትህ አካላት ህንፃ ግንባታ ያለበትን የጥራት ደረጃ አድንቀው በአጠረ ጊዜ ውስጥ የክፍያ ጥያቄዎችን አንደሚፈቱ እና ውሳኔ እንደሚያገኙ መግለጻቸውን ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review