የፍትህ ስርዓቱን ታማኝ እና ግልፅ በማድረግ የተጀመሩ ውጤታማ የምርመራ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል- ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ

You are currently viewing የፍትህ ስርዓቱን ታማኝ እና ግልፅ በማድረግ የተጀመሩ ውጤታማ የምርመራ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል- ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ

AMN-ጥር 16/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የ2017 ዓ.ም የ6ወር የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ፣ ተቋማዊ ዕቅዱን ለማሳካት የፍትህ ስርዓቱን ታማኝ እና ግልፅ በማድረግ የተጀመሩ ውጤታማ የምርመራ ሥራዎችን በታክቲክ ፣በፎረንሲክና በድጋፍ ውጤት የተገኘባቸውን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የግማሽ በጀት አመቱ የተሻለ የመዝገብ አፈፃፀም የተመዘገበበት መሆኑን በመግለጽ በተለይም በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች በመንግስት እና በህዝብ ሀብት ላይ በደረሰ ጉዳት የምርመራ መዝገቦችን እያጣሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ6ወር የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review