የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብ ሊኖራቸው እንደሚገባ የፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ዋና ተደራዳሪ የነበሩት እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።
አምባሳደሩ ፓርቲዎች አዲሱን ትውልድ ማቀፍ እንዲችሉ ትናንት የነበሩ እሳቤዎች ላይ ብቻ ሙጥኝ ከማለት ሊቆጠቡ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የፖለቲካ እሳቤዎችን በዘመናት ሂደት ባስገኙት ውጤት እየመዘኑ የተሻለውን እያላቁ፣ የጎደለውን አየሞሉ እና ጨርሶ መተው የሚገባውን እየተዉ መሄድ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አምባሳደሩ “አንድ ፓርቲ ከቃላት ጭምር ምንም ነገር ሳይቀይር መኖሮ ከቻለ ፤ ለአሁኑ ትውልድ ምንም እርባና የለውም ማለት ነው” ብለዋል።
የፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ዋና ተደራዳሪዎች የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡