AMN-ጥቅምት 30/ 2017 ዓ.ም
በመከላከያ ስልጠና ዋና መምሪያ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖች የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ ይከናወናል።
ተመራቂ ዕጩ መኮንኖች በማሠልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩና የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና ወሥደው ያለፉ መሆናቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመልክቷል።