ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በህንድ እና ፓኪስታን መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing ዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በህንድ እና ፓኪስታን መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም

በካሽሚር የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በጎረቤት ሃገራቱ ህንድ እና ፓኪስታን መካከል ያለው አለመግባባት ተባብሶ አለም አቀፍ ስጋት ፈጥሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ሽብርተኝነትን በማውገዝ ከሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና እንደ ኩዌት እና ሳዑዲ አረቢያ ያሉ ሀገራትም የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ህንድ ለጥቃቱ ከፓኪስታን ጋር የተገናኙ ቡድኖችን ተጠያቂ ያደረገች ሲሆን እንደ የውሃ መጋራት ያሉ ቁልፍ ስምምነቶችን በማቋረጥ ወታደራዊ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ፍንጭ ሰጥታለች። ፓኪስታን በበኩሏ የጥቃቱን ክስ ያስተባበለች ሲሆን ህንድ ጥቃት ለማድረስ እንዳቀደች በመክሰስ ለአጸፋ ምላሹ እርሷም አስጠንቅቃለች።

ሁለቱም ወገኖች ጠንከር ያለ ንግግር እና የድንበር የተኩስ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ግጭትን ለመከላከል ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ማጠናከሯን ቢቢሲ በዘገባው አካቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review