AMN – የካቲት 3/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ምሽትን ተገን በማድረግ የቆሸሸ ውሃ አዲስ ወደ ተሠራው አስፓልት የለቀቀው የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት 300 ሺህ ብር በመቅጣት ያቆሸሸውን አካባቢ እንዲያጸዳ ተደርጓል ፡፡
ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን ፣ ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ማቅረቡን የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን በመረጃው አመልክቷል፡፡