የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዩክሬኑ አቻቸዉ ቮሎድሚር ዘለንስኪ በሮማዉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የሰንብት መርሃ ግብር ላይ ተገናኝተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች ስኬታማ ነዉ የተባለለትን ውይይት ማድረጋቸዉን የነጩ ቤተ መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
መሪዎቹ ለ15 ደቂቃ ያህል የተወያዩባቸዉ አበይት ጉዳዮች ወደፊት የሚገለጹ መሆናቸዉን ነዉ የዋይት ሀውስ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሯ ስቲቨን ቼንግ የገለጹት፡፡
ዶናልድ ትራምፕና ዘለንስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦቫል ኦፊስ የተገናኙ ሲሆን ዉይይታቸዉም ከፍተኛ ዉጥረት የታየበት ነበር፡፡
ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የሰንብት መርሃ ግብር ጎን ለጎን ያካሄዱት ሁለተኛዉ ዉይይት ግን የሰከነ እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ እና ቮሎድሚር ዘለንስኪ የዩክሬንና ሩሲያን ግጭት ለማስቆም ጥረቶች እየተደረጉ ባለበት ወቅት ነዉ ሁለተኛዉን ዉይይታቸዉን ያካሄዱት፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ