በትናንትናው ዕለት ነዋሪዎች ከቴህራን ፈጥነው እንዲለቁ ትዕዛዝ የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ለእስራኤል-ኢራን ግጭት ከተኩስ አቁም የተሻለ መፍትሄ እየፈለግን ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ሀሳቡን የሰነዘሩት ከቡድን 7 ዓባል ሀገራት ስብሰባ አቋርጠው ከወጡ በኋላ ሲሆን፣ ምን ለማለት እንደፈለጉ ግልጽ አለመሆኑ ተነግሯል፡፡
አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የእስራኤል እና ኢራን ጦርነት እንደቀጠለ ነው፡፡
የእስራኤል ጦር ኢራን ትናንት ሌሊት 30 ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች ማለቱን ተከትሎ፣ በኢራን ርዕሰ መዲና ፍንዳታዎች እየተሰሙ መሆኑን የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን መግለጹ ተነግሯል፡፡
የቴህራን ጎዳናዎችም ከተማውን ለቀው ለመውጣት በሚተራመሱ ነዋሪዎች መጨናነቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በታምራት ቢሻው