ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ ከ12 ሀገራት ወደ ዩኤስኤ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚከለክል ሰነድ ፈረሙ

You are currently viewing ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ ከ12 ሀገራት ወደ ዩኤስኤ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚከለክል ሰነድ ፈረሙ

AMN – ግንቦት 28/2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አፍጋኒስታንን፣ ሃይቲን እና ኢራንን ጨምሮ ከ12 ሀገራት ወደ ዩኤስኤ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚያከለክል ሰነድ መፈረማቸው ተገለጸ።

ክልከላው ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኤርትራ፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና ሱዳንንም ያካትታል።

በተጨማሪም፣ ኩባን እና ቬኑዙላን ጨምሮ በሌሎች ለጊዜው ስማቸው ይፋ ባልተደረጉ ሰባት ሀገራት ላይም ተፈጻሚ የሚሆን የጉዞ ገደብ ይፋ ማድረጋቸውም ተመላክቷል።

የጉዞ ክልከላው እና እግዱ ያስፈለገበት ምክንያትም፣ የአሜሪካን ደህንነት እና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ክልከላው አትሌቶችን ጨምሮ ለታወቁ የእስፖርታዊ ጉዳዮች ለሚጓዙ አንዳንድ የአፍጋኒስታን እና ጥምር ዜግነት ላላቸው ከነዚህ ሀገራት ውጪ የሚኖሩትን እንደማያካትት አልጀዚራ ዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሺያል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክትም፣ የኮሎራዶውን ጥቃት ጠቅሰዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሊተገብሩት ቃል ከገቡበት እና ከሰኔ 9 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ የጉዞ ክልከላ የህግ ጫናዎችን ሊፈጥር እንደሚችል ከወዲሁ ተሰግቷል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review