ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ከኢራን ጋር አፋጣኝ ውይይት ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለፁ

You are currently viewing ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ከኢራን ጋር አፋጣኝ ውይይት ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለፁ

AMN – ሰኔ 08/2017 ዓ.ም

ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ ከኢራን ጋር አፋጣኝ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን የጀርመኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሃን ዋዴፉል ተናግረዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ዮሃን ዋዴፉል በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ግጭት ለማርገብና የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀው፣ ቴህራን ከዚህ ቀደም የቀረበላትን የገንቢ ውይይት እድል መጠቀም እንዳልቻለች ጠቁመዋል።

ጀርመን ከፈረንሳይ እና ብሪታኒያ ጋር በመሆን ያቀረበችው የውይይት ሃሳብ ተቀባይነት ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ጦርነቱን ማስቆም የሚቻለው በኢራን እና እስራኤል ላይ በሁሉም አቅጣጫዎች ጫና ማሳደር ሲቻል ብቻ እንደሆነም መጠቆማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review