AMN_የካቲት 12/2017 ዓ.ም
የሪያል ማድሪዱ አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም ሪያል ማድሪድ ከኦሳሱና አንድ አቻ በተለያየበት የላሊጋዉ ጨዋታ በሰራዉ ጥፋት እና አላስፈላጊ ንግግር ተናግረሀል በሚል የእለቱ ዳኛ ጆሴ ሞንቴሮ በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዳስወጡት የሚታወስ ሲሆን ማድሪድ በላሊጋዉ ከጅሮና እና ሪያል ቤቲስ ጋር በሚያደርጋቸዉ ጨዋታዎች እንደማይሰለፍ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
የስፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ባደረገዉ ስብሰባም ተጫዋቹ ዳኛዉ ላይ ባሳየዉ ያልተገባ ባህሪ ቅጣቱን ማስተላለፉ የተገለፀ ሲሆን ዳኛዉ ነግሩን ካለመረዳት የተነሳ እንጂ አላስፈላጊ ቃላት አለመናገሩን ተጫዋቹ ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡
ሪያል ማድሪድም በጉዳዩ ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን የ21 አመቱ እንግሊዛዊ በዛሬዉ ጨዋታም ላይሰለፍ ይችላል ተብሏል፡፡
ቤሊንግሀም በሪያልማድሪድ 33 ጨዋታዎችን አድርጎ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር 10 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡
በአልማዝ አዳነ