የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፕሮስቴት ካንሰር መያዛቸው ተገልጿል።
የ82 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በተደረገላቸው ምርመራ በፍጥነት በሚዛመት የፕሮስቴት ካንሰር መጠቃታቸው መረጋገጡን ቢሯቸው አስታውቋል።
ቢሮው ካንሰሩ ወደ አጥንታቸው ጭምር መዛመቱን መግለጹን ተከትሎ ፤ የካንሰሩ ስርጭት በህክምና ሙያተኞች ልየታ ‘ከፍተኛ ደረጃ’ እንደሚያርፍ ቢቢሲ ዘግቧል።
ካንሰሩ ሆርሞን ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሊታከም አንደሚችልም ቢሮው ይፋ አድርጓል።
የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ እና ቤተሰቦቻቸው የተሻሉ የህክምና አማራጮችን በማጤን ላይ መሆናቸውም ተመላክቷል።