ጊዜው ለከተማዋ አመራር ወርቃማ ዘመን ነው፡-የምክር ቤት አባላት

You are currently viewing ጊዜው ለከተማዋ አመራር ወርቃማ ዘመን ነው፡-የምክር ቤት አባላት

AMN – የካቲት 12/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ እያከናወነች ያለው የልማት ስራዎች የሚደነቁ እና በዚህም ለከተማዋ አመራር ወርቃማ ዘመን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ያለፉት 6 ወራት ሪፖርት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ ሰሞኑን በከተማዋ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸው በጉብኝታቸው የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች የሚያስገርሙ እና የሚደነቁ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ኑሮ መቀየር የሚችሉ እና ማህበረሰቡ ላይ ውጤት ያመጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በኮሪደር ልማቱ ለልማት ተነሺዎች በተሰራው ስራ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፣በቅድመ ወሊድ እና ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረጉ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እጅግ እንዳስገረሟቸው በጉብኝታቸው ወቅት መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በገላን ጉራ የተመለከትነው የልማት ስራ በእጅጉ አስገርሞናል ያሉት የምክር ቤት አባላቱ የልማት ስራው የሚታይ የሚጨበጥ እና የሚዳሰስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በገላን ጉራ የካዛንችስ የልማት ተነሺዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች፣ ሱቆች እና ሌሎች የልማት ስራዎች በ57 ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸው የሚያስገርም መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በተለይም 120 ሜትር ስፋት ያላቸው የ136 ኪሎ ሜትር የመንገድ ልማት ስራ ከአንደኛው ዙር የኮሪደር ልማት በበጠ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ ኢንተርናሽናል ኤግዚቢሽን እና የኮንቬንሽን ማእከል ፣የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎች እና ሌሎች የልማት ስራዎች እጅግ የሚያስገርሙ እና የአገሪቱን የብልጽግና ጉዞ የሚያሳኩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የከተማ አስተዳደሩ አመራር ክትትል እና ድጋፍ ከፍተኛ እንደሆነ እና ይህም የአመራሩ ወርቃማ ጊዜ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪም ለልማቱ ስራ ተባባሪ በመሆን ያበረከተው አስተዋጽኦ የሚያስመሰግነው መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡ ትውልዱ ከዚህ ስራ ትልቅ ትምህርት ሊወስድ እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡

ይሁን እና አሁንም የኑሮ ውድነቱን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ያለው ስራ በጣም ጥሩ ቢሆንም አሁንም በተሻለ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይም በአገር ውስጥ ምርቶች የዋጋ ንረት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

የገርቢ ውሀ ፕሮጀክት ስራ ሊፋጠን እንደሚገባው ያሳሰቡት የምክር ቤት አባላቱ የስራ እድል ፈጠራ ላይ የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም ከስራ ፈላጊ ወጣት አኳያ ተጨማሪ ስራ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

የግንባታ ስራ ፍቃድ አሰጣጥን ማቀላጠፍ፣ መምህራንን በስልጠና ማብቃት�እና የአርሶ አደር ይዞታ ማረጋጋጫ መስጠት ላይ ያሉ ክፍተቶችን መሙላት እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን ማሟላት ላይ ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በሰለሞን በቀለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review