ጊዜያዊ ችግሮቻችንን በመረዳዳት እየተሻገርን ለዘላቂ ልማታችን ደግሞ 24/7 በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ጊዜያዊ ችግሮቻችንን በመረዳዳት እየተሻገርን ለዘላቂ ልማታችን ደግሞ 24/7 በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ 25ኛውን እና 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከፍተው አገልግሎት አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2014 ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት ለሚቸገሩ ወገኖችን 24 የምገባ ማዕከላትን በመክፈት ንፁህ፣ ጤናማ እና ትኩስ ምግብ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ወገኖች እየመገበ መሆኑ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለትም የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለከተማ ጉራራ አካባቢ 25 ኛውን እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ደግሞ 26 ኛውን የምገባ ማዕከል ከፍተው አገልግሎት አስጀምረዋል።

ዛሬ ስራ የጀመሩት እነዚህ የምገባ ማእከላት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በመጠለያ ይኖሩ የነበሩ እና ምንም ገቢ የሌላቸዉ አቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ለማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ያሉበት አካባቢ በመሆኑ እነሱን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

25ኛውን የምገባ ማዕከል የገነቡትን እንዲሁም የምገባውን ወጪ የሚሸፍኑትን አያት አክሲዮን ማህበርን እና የኢፌዴሪ የጉምሩክ ኮሚሽንን አመስግነዋል፡፡

ጊዜያዊ ችግሮቻችንን በመረዳዳት እየተሻገርን ለዘላቂ ልማታችን ደግሞ 24/7 በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን ሲሉም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review