ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው ድርጅት 100 ሺህ ብር ተቀጣ

You are currently viewing ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው ድርጅት 100 ሺህ ብር ተቀጣ

AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ግንፍሌ ወንዝ ውስጥ ቆሻሻ የጣለው የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ቤተክነት የሠንበት ት/ቤት ማደራጃና መምሪያ የማህበረ ቅዱሳን ተቋም በከተማ አስተዳደሩ የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 በመተላለፍ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ወንዝ በመጣሉ 100 ሺህ ብር ተቀጥቷል።

ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተደደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን እና በመድረኮች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠሩ ይታወሳል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ዙሪያ ደንብ የሚተላለፉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማሳወቁን ከባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review