ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክተ ዛሬ ወንድሜን አሊኮ ዳንጎቴን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስችሉ ስልታዊ የኢንቬስትመን መስኮች ላይ ውይይት አድርገናል። ትብብራችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡