ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ማካሄዳቸዉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ጥበባት ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ናቸው። ባሕላዊ ሀብትን ጠብቀው ያቆያሉ። ለማኅበራዊ አንደነት አበክረዉ በመስራትም ብዝኃነት ላላቸው ማኅበረሰቦች ድምፅ ይሆናሉ።
በትምህርት ረገድም ጥበባት ፈጠራን እና ምክንያታዊ አስተሳሰብን ያሳድጋሉ ሲሉ ገልጸዋል።
በኢኮኖሚ ረገድም ጥበባት ፈጠራን፣ ቱሪዝምን እና ስራ ፈጠራን የመምራት አቅምም አላቸው።

ዛሬ ጠዋት ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደናል።
ተወካዮቹ በተለያየ ደረጃ እየተካሄደ በመጣውና በዘርፉ ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመለየት በረዳው ሰፊ የውይይት መርሃግብር የተሳተፉ ናቸው።
የዛሬው መድረክም የውይይት ግኝቶቹን በማጠናከር የከፍተኛ አመራሩን ትኩረት እና መፍትሔ የሚሹ እንዲሁም በዚህ መስክ የተሰማሩ አካላት ሚናቸውን የሚወጡባቸው ጉዳዮችን በመለየት ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።