ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

AMN ግንቦት 20/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።

ኢንስትትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው። የምርምር ስራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመትንበያና የትንበያ ስራዎችን በመስራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል።

የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ ሲሆን ዛሬ በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ስራዎች ምልከታ መደረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review