AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የአፍጥር ሥነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየአመቱ የሚያከናውኑትን የአፍጥር መርሃ ግብር በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በቅርቡ በታደሰው ብሔራዊ ቤተመንግሥት አከናውነዋል።
የአፍጥር ተሳታፊዎች ብሔራዊ ቤተመንግሥቱንም መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለከታል።