AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በዋና ዋና የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ውይይታቸውን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ፣ ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረጅም ታሪክ እና ጥልቅ ግንኙነት አላቸው ብለዋል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ነው ያሉት።
ወደ ፊት ስንመለከት፣ አጋርነታችን ከፖለቲካ እና ከዲፕሎማሲ በላይ በመስፋፋት ከፍተኛ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ይጨምራል ሲሉም ገልጸዋል።