AMN – የካቲት 8/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የክትባት ድጋፍ ሰጪ አጋር ተቋም (GAVI) ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳኒያ ኒሰህታር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር ግንኙነቷን ማጠናከር በምትችልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለይም አገሪቱ ስለሚኖራት ስር ነቀል የጤና እቅድ ላይ በጥልቀት እና በትኩረት መወያየታቸውን በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ጠቅሰዋል፡፡