መነሻዋን ከጅቡቲ ዶራሌህ ወደብ አድርጋ ሶስት ወራት ለተጠጋ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ስትጓዝ የቆየችው ጣናነሽ 2 ጀልባ አዲስ አበባ ደርሳለች።
150 ሜትሪክ ቶን ክብደት እና 38 ሜትር እርዝማኔ ያላት ጀልባዋ፣ አዲስ አበባ ስትደርስ ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል አድርጎላታል።
ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ ፅናት በታከለበት ብርቱ የትብብር ስራ እዚህ መድረሷ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
ከመነሻዋ ጀምሮ ጀልባዋን እያጓጓዙ የሚገኙት አሽከርካሪዎች፣ የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ ለሀገራቸው የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት በመቻላቸው ከፍተኛ ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
188 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላት ጀልባዋ፣ የጣና ሃይቅን የቱሪዝም እንቅስቃሴ በማሳለጥ ረገድ የሚኖራት ሚና የጎላ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በመቅደስ ደምስ