ጣና ነሽ ፪ እና አነስተኛዋ ጀልባ ወደ ሀገር ቤት እያቀኑ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ጣና ነሽ ፪ እና አነስተኛዋ ጀልባ ወደ ሀገር ቤት እያቀኑ መሆኑ ተገለጸ

AMN – መጋቢት 12/2017

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጭነው ወደ ሀገር ቤት በማምራት ላይ መሆናቸዉን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ፡፡

ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ 38ሜ እርዝመት እንዳላት እና በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም አላት፡፡

ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ እንደሆነች ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review