
AMN-ኅዳር 8/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአድዋ ሲኒማ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉን ባለ ቀለም ፊልም “አስቴር “ ዲጂታላይዝ በማድረግ አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በታደሙበት በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ከንቲባዋ ይህንን አስመልክተው በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፣ “ጥበብ ሀገርን በማነፅ ጉዞ ውስጥ አይነተኛ ሚና አላት” ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዘርፉ የሀገሪቱን የልዕናልና ጉዞ ሊያሳልጥ እንዲችል የኪነ-ጥበብ መሰረተ ልማቶችን ገንብቶ ለህዝቡ ጥቅም ማቅረቡን ጠቁመዋል።
ይበልጥ የማስፋፋቱ ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንዲጠቀሙበትም ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።