ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለተመራው ልዑክ የእራት ግብዣ አደረጉ

You are currently viewing ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለተመራው ልዑክ የእራት ግብዣ አደረጉ

AMN – መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ እና ለልዑካን ቡድናቸው የዕራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ለሩዋንዳው ኢታማዦር ሹም እና ለልዑካቸው የኢትዮጵያን የባህል አልባሳትና ልዩ ልዩ ስጦታዎችንም አበርክተውላቸዋል።

በተመሳሳይ የሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአድዋ ጅግኖችን የሚያስታውስ ጋሻና ጦር የያዘ ምስልና የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review