የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋንጋ በክብር ዘብ የታጀበ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መካከል የሁለትዮሽ የጋራ ውይይት ተካሂዷል።
ጉብኝቱ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ እንድምታ ያለው መሆኑን እና ሁለቱ አገራት በመከላከያ እና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ በአዳዲስ የትብብር መስኮች ለመሥራት እና የቀጠናውን ሰላም እና ደህንነትን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው ተብሏል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጉብኝታቸው ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መኖር ስላለበት ግንኙነትና ትብብር በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም ከሩዋንዳው መከላከያ ሚኒስትር ጁቬናል ማሪዛሙንዳ ጋርም ተነጋግረዋል።