“ፋይዳ ለኢትዮጵያ ” 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው

You are currently viewing “ፋይዳ ለኢትዮጵያ ” 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ ነው

AMN- ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

“ፋይዳ ለኢትዮጵያ ” 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡

መርሐ-ግብሩን አስመልክቶ፣ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር የጋራ መግለጫ ተሰጥቷል።

በፋይዳ ምዝገባ ላይ ያለውን የህብረተሰብ ግንዛቤ እና አረዳድ በስፖርት ንቅናቅኔ ማጠናከረ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ “ፋይዳ ለኢትዮጽያ ” በሚል መሪ ሀሳብ የጎዳና ላይ ሩጫ በመስቀል አደባባይ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግረዋል።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርዓያ ስላሴ በመግለጫው እንደገለፁት፣ ሩጫው የምዝገባ ንቅንናቄውን ያግዛል ተብሎ የታመነበትና የፋይዳ ምዝገባን በህብረተሰቡ ውስጥ በስፋት ለማስረፅ በሌሎች ክልሎችም ይህ የስፖርት ንቅናቄ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ ለሯጮች የሚሰጠው ቲ-ሸርት ነፃ መሆኑን እና ለሁሉም ተወዳዳሪዎች ሜዳልያ ሽልማት እንደሚኖር የገለፁ ሲሆን በወንዶች ፣ በሴቶች እና በፓራ ለሚወዳደሩ አሸናፊ አትሌቶች በየደረጃው ሽልማት እንደተዘጋጀም ጠቁመዋል።

በፂዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review