ፑቲን በሩሲያ-ዩክሬን ድርድር ላይ ሳይገኙ ቀሩ

AMN ግንቦት 07/2017

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር በምታደርገው የሰላም ድርድር ላይ በአካልሳይገኙ መቅረታቸው ተገልጿል፡፡

የሰላም ድርድሩ ላይ ለመካፈል ቱርክዬ የገቡት የዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚር ዘለንስኪ፤ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በመምከር ላይ ይገኛሉ፡፡

በድርድሩ ላይ በአካል እንደሚገኙ ሲጠበቁ የነበሩት ፕሬዚዳንት ፑቲን ፤ በእርሳቸው ፈንታ እንደራሴዎቻቸውን መላካቸው ዘለንስኪን ሳያስቆጣ እንዳልቀረ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በግንባር ካልሆነ በቀር ለድርድር አልቀመጥም ማለታቸው ይታወሳል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እኔ እና ፑቲን በአካል ያልተገኘንበት የሰላም ድርድር አይሰምርም ሲሉ ለጋዜጠኞች መናገራቸውም ተመላክቷል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review