AMN – የካቲት 20/2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ መልዕክት፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ናሚቢያን ወደ መካከለኛ ገቢ ያለው ሀገር ያሻገሩ መሪ ይባሉ እንደነበር አመላክተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ፣ ሳም ኑጆማ የናሚቢያ መስራች አባት እና ሀገራቸውን የቀየሩ መሪ ነበሩ ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡