ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ጥቃት የመሰንዘሩን ጉዳይ እያሰቡበት እንደሆነ ገለጹ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ላይ ጥቃት የመሰንዘሩን ጉዳይ እያሰቡበት እንደሆነ ገለጹ

AMN- ሰኔ 12/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም የያዙትን እቅድ ቢያፀድቁም፣ የመጨረሻውን ውሳኔ እያመዛዘኑ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ለኢራን የኒውክሌር መርሐ-ግብር አስፈላጊ የሆነውና ከመሬት ሥር የሚገኘውን የፎርዶ ኒውክሌር ማበልጸጊያ ማዕከልን የማውደም ችሎታ ያላት አሜሪካ ብቻ እንደሆነች ነው የሚነገረው።

ዕቅዳቸውን አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ የሰጡት ምላሽ፣ በብዙዎች ዘንድ ለትርጉም የተጋለጠ ሆኗል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በምላሻቸው፣ “ላደርገውም ላላደርገውም እችላለሁ” ያሉ ሲሆን፣ ላደርግ የምፈልገውን ማንም አያውቅም በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም አንድ ነገር ማለት እንደሚችሉ በመግለጽ፣ ኢራን ብዙ ችግር ስለገጠማት መደራደር እንደምትፈልግ አመላክተዋል።

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ ዓርብ ዕለት ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከጀርመን እና ከፈረንሳይ አቻዎቻቸው ጋር በጄኔቫ በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ለመገኘት ማሰባቸው ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እስራኤል በአራክ እና በካንዳብ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በማዘዝ፣ በቴህራን ሌላ ምሽት ተከታታይ ጥቃት መፈጸማዋን እንደቀጠለች ቢቢሲ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review