የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 530 ሺህ ለሚሆኑ ኩባውያን፣ ሃይቲያውያን እና ሌሎችም ስደተኞች የህግ ከለላ ማንሳታቸው ተነገረ፡፡
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከግማሽ ሚሊዮን ለሚልቁ ኩባውያን፣ ሃይቲያውያን፣ ኒካራጋውያን እና ቬንዙዌላውያን የህግ ከለላቸውን ማንሳቱ ተገለጸ፡፡
እነዚህ ሥደተኞች በመንግስት ይፋ በሆነው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ማለትም እስከ ፈረንጆቹ ሚያዚያ 24 ቀን 2025 ድረስ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ጊዜ ከመሰረዙ በፊት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
እነኚህ 530 ሺህ ስደተኞቹ ወደ አሜሪካ ግዛት የተወሰዱት በጆ-ባይደን የአስተዳደር ዘመን (CHNV) በተሰኘ የድጋፍ መርሓግብር ለስደተኞች የተከፈተ ህጋዊ መንገድ እንደነበረም ተገልፆአል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቢሮአቸውን እንደተረከቡ ይህንን መርሓግብር ማገዳቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡
ከእነዚህ ሥደተኞች ውስጥ በጊዜያዊነትም ቢሆን ምን ያህሉ አሜሪካ ውስጥ እንዲቆዩ የሚያስችላቸው ህጋዊነት እንዳለ ማረጋገጥ እንዳልቻሉ የቢቢሲ ዘገባ ያሰረዳል፡፡