
AMN – ታኅሣሥ -3/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰው የአንካራ ስምምነት በአገራቱ መካከል እና በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ ቀጣናዊ ትብብር መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ በኤክስ ገፃቸው አስታወቁ።
የኢትዮጵያን እርምጃ ትክክለኛ መሆኑን ያመለከቱት ፕሬዝዳንት ታዬ ስምምነቱ ከቀጣናው ባሻገር ያለው ፋይዳ ወሳኝ መሆኑንም አመልክተዋል ፡፡
በተርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አቀራራቢነት ትናንት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል።