ፖለቲካዊ አመለካከቶች እንዳሉ ሆነዉ በሀገራዊ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ገለጹ።

You are currently viewing ፖለቲካዊ አመለካከቶች እንዳሉ ሆነዉ በሀገራዊ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ገለጹ።

AMN – ሰኔ 12/2017 ዓ.ም

ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ አባላት በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘውን የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ጎብኝተዋል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የጠቆሙት የፖለቲካ ፖርቲ አባላቱ፤ ፕሮጀክቱ እጅግ ግዙፍ እና ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሀብት ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።

የግንባታ ሁኔታው ትልቅ ምሳሌ እንደሆነ እና የግንባታው ደረጃም ከገመቱት በላይ ሆኖ እንዳገኙት ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ የተባበሩ ክንዶች ውጤት ማሳያ መሆኑን እና የሀገርን ሀብት በመለየት በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል ከተቻለ ሀገር በአጭር ጊዜ እንደምትለወጥ አመላክተዋል።

ፖለቲካዊ አመለካከቶች እንዳሉ ሆነዉ በሀገራዊ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት የተጎበኘው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ሲገባ 1800 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።

ይህም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ከፍተኛ ኃይል አመንጪ ግድብ ያደርገዋል።

‎በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክቱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ መካከል ላይ ይገኛል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ 65 በመቶ መጠናቀቁን የገለጹት አስተባባሪዎች፥ ፕሮጀክቱን ‎ወደ ፍፃሜው ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review