ከኢትዮጵያ ፖሊስ አባላት የሚጠበቀው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፣ሰላም እና አንድነት የማረጋገጥ ስራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በ116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ብሔራዊ ቀን በአል አከባበር መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 116 አመታት ለአንድ ተቋም ቀላል ትርጉም የሚሰጠው ባይሆንም ይህን ያክል አመት መቆየት በራሱ ጠቀሜታ እንዳለዉ ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት የለዉጥ አመታት በኢትዮጵያ ተቋም ግንባታ ውስጥ የፖሊስን ተቋም የሰላም እና የደህንነት ጠባቂ ለማድረግ የተሰራው ስራ አመርቂ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም ከደረሰበት ሁኔታ አንፃር አሁንም በቀጣይነት መሰልጠን፣ መታጠቅ፣ መዘጋጀት ከሁሉም ሰራዊት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ከፖሊስ አባላት የሚጠበቀው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፣ሰላም እና አንድነት የማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ለዘላለም ታፍራና ተከብራ ትኖራለች፤አንድነቷና ሰላሟ ይጠበቃል፤ ብልፅግናዋም ይረጋገጣል ሆኖም ግን፣ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት የማይሹ አካላት በተለመደው መንገድ በክንዳችን ይፈርሳሉ፤እኛም ፀንተን እንኖራልን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአስማረ መኮንን