10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ዉድድር ተጀመረ

You are currently viewing 10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ዉድድር ተጀመረ

AMN – መጋቢት 13/2017 ዓ.ም

10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ዉድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም በይፋ ተጀምሯል፡፡

የውድድሩ ዋና አላማም ትምህርት ቤቶች ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት የሚፈሩባቸው ተቋማት በማድረግ የኢትዮጵያን የስፖርት ትንሳኤ ማረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል ።

ውድድሩ በአንደኛ እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁለቱም ጾታዎች በ6 የስፖርት አይነቶች፣ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች በ10 የስፖርት አይነቶች ይደረጋል ተብሏል።

በመምህራን ደረጃ ዉድድሩ በ5 የስፖርት አይነቶች የሚደረግ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ከ30 ሺ በላይ የትምህርት ማህበረሰብ በተገኘበት በአዲስ አበባ ስታድየም የሚከፈት ተከፍቷል።

በመክፈቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን ፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ተገኝተዋል ።

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review