10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በሐረር ከተማ እየተከበረ ነው

You are currently viewing 10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በሐረር ከተማ እየተከበረ ነው

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን አከባበር መርሃ ግብር በሐረሪ ክልል እየተካሄደ ነው።

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምረው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በየዓመቱ እንዲከር በወሰኑት መሰረት ዘንድሮም 10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በሐረሪ ክልል እየተከበረ ይገኛል።

“አሥር የትምህርት ቤት ምገባ ዓመታት፤ ያለፈውን ስኬት እናክብር፤ መጪውን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዕለቱ በከተማው በሚገኘው አንድ ሞዴል የ1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተካሄደ የሚገኘውን የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር ተዘዋውረው መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

9ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት የምገባ ቀን ባለፈው ዓመት በድሬደዋ አስተዳደር መከበሩ ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review