116ኛው ፖሊስ ምስረታ በዓል በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች እየተከበረ ሲሆን፣ የዚሁ አካል የሆነው ስነ -ስርዓት ነገ ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚደረጉ የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች ይከበራል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህም መሠረት፦
-ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ (22 አደባባይ በተመሣሣይ ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ)
-ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ)
ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
-ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት
ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ)
-ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
-ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት ( ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ጋዜቦ ላይ )
-ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ
-ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት (ሜክሲኮ አደባባይ ላይ)
-ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ )
-ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ )
-ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ ላይ )
-ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ እንደሚሆኑ መረጃው አመላክቷል።
በተጨማሪም፦
-ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
-ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
-ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
-ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
-ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
-ከብሔራዊ ቤተጰመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ሲሆን፣ እንዲሁም ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።