116ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነዉ

You are currently viewing 116ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነዉ

AMN- ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም

116ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ቀንን ሚያዚያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፌደራል ፖሊስ ገለጸ፡፡

በዓሉን አስመልክቶም ከሚያዝያ 19 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር በአበበ ቢቂላና በአዲስ አበባ ስታዲየም በሰባት ሀገራት መካከል እንደሚካሄድም ተገልጿል።

እንዲሁም የሀገር ውስጥና የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት አባል ሀገራት የፖሊስ ምሁራን የሚሳተፉበት ሲምፖዚየም ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በፖሊስ ታሪካዊ አመጣጥ እና በፖሊስ ሪፎርም ስኬቶች ላይ ያተኮረ አውደ-ርዕይም ከሚያዚያ 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ እይታ እንደሚበቃ ለማወቅ ተችሏል።

የክልል ፖሊስ ተቋማትም በዓሉን በከተማ አስተዳደር እና በክልል ደረጃ ለማክበር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለጹን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የዕቅድ አፈፃፀም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየገመገመ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review