117 ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው

You are currently viewing 117 ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው

AMN-ጥቅምት 15/2017 ዓም

117ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት!” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት በሃገር ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ወታደራዊ አታሼዎች የሠራዊቱን ታሪካዊ የጀግንነት አመጣጥ እና ያለፋቸውን ፈተናዎች እንዲሁም አሁን ላይ ሠላም እያሰፈነ የዘመናዊነት ግንባታ ሂደቱን እያረጋገጠ የሚሻገር ሠራዊት መሆኑን የሚያመላክት የፖናል ውይይት ተደርጓል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሠው ሠራሽና ተፈጥሯዊ መሠናክሎች ሳይበገር ባሕር ተሻግሮ የመጣን ጠላትም ሆነ የውስጥ ችግር ፈጣሪ ባንዳን እንደ አመጣጡ በመመለስ የሀገሩን፣ የሠንደቅ ዓላማውን እና የህዝቡን ክብር ያሥጠበቀ የሠላምና የልማት ኃይል የሆነ ሠራዊት መሆኑ ተገልጿል።

በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ራሱን እያሳደገና ጠላቱን እየመከተ አቅሙን እያጎለበተ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፣የሀገሩን ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ሁለንተናዊ ዝግጁነት እየገነባ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review