129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት ይከበራል

You are currently viewing 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዛሬው ዕለት ይከበራል

AMN – የካቲት 23/2017 ዓ.ም

በዓሉ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በተቋማት፣ በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽ/ቤቶች ይከበራል።

በአዲስ አበባ ከተማም 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን የአከባበር ሥነ-ሥርዓቱም በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ እንደሚጀመር ነው የተመላከተው፡፡

በመርሐ ግብሩ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙም ተገልጿል፡፡

በአርበኞች እና በአሁኑ ትውልድ መካከል የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ እንደሚደረግ እና የዓድዋ ድል በዓልን የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብም የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review