ዛሬ በተጀመረዉ ሻምፒዮና የተለያዩ የፍፃሜና የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል::
በሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል በተደረገ የፍፃሜ ውድድር አለምናት ዋለ ከአማራ ፖሊስ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡
ኬና ቱፋ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 2ኛ ፤ ዘሪቱ ዳባ ከሸገር ሲቲ 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል::
በወንዶች በተደረገ 3000 ሜትር መሰናክል ዲንቃ ፍቃዱ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ቀዳሚ ሆኖ መግባት ችሏል::
ሀይሉ አያሌው ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 2ኛ ፤ ጀማል ጁሀር ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 3ኛ ደረጃ ይዘው ጨርሰዋል፡፡
የጦር ውርወራ በሁለቱም ፆታ ፤ በወንዶች ከፍታ ዝላይ የፍፃሜ ውድድሮች ተደርገዋል፡፡
የውድድሩ የከሰዓት መርሃግብር ከ10 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በአዲሱ መንገሻ