AMN -ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
15ኛውን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚኒስትሮች ምክርቤት ስብሰባ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል የዝግጅት ኮሚቴ ከተለያዩ ተቋማት ተውጣጥቶ ስራ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ጠዋት የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም ይበልጥ በሚጠናከርበት አግባብ ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን አስታውቀዋል::