አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ( ኤ ኤም ኤን )መስከረም 7/2016 ዓ.ም
ሰባት ክለቦች የሚሳተፋበት የዘንድሮው 17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታድየም ተጀምሯል።
ውድድሩን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እና የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ደረጀ አረጋ በጋራ ያስጀመሩ ሲሆን በውድድር መርሀግብሩ መሠረት የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ የሆነው የሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ተጀምሯል።
17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በሁለት ምድብ የሚካሄድ ሲሆን በምድብ ሀ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ሻሸመኔ ከተማ የተደለደሉ ሲሆን በምድብ ለ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን መደልደላቸው ይታወሳል።
በአብርሃም አድማሱ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ