18ኛው የባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

You are currently viewing 18ኛው የባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

AMN – የካቲት 30/2017 ዓ.ም

22ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር አካል የሆነው ፌስቲቫሉ ዛሬ በሆሳዕና አብዬ ስታዲየም ተጀምሯል።

የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሕይወት ሞሃመድ በስፍራው ተገኝተው ፌስቲቫሉን አስጀምረዋል።

በዛሬው ዕለት መርሐ ግብር የተያዘላቸው ሦስት ክልሎች ውብ የሆነ ባህላዊ ዕሴታቸውን ለታዳሚያን አሳይተዋል። ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሐረሪ እና ሲዳማ ክልሎች በስታዲየም ለተገኙ በርካታ ተመልካቾች እና ለዳኞች ትርዒታቸውን አቅርበዋል።

የባህል ፌስቲቫሉ ሁሉም ተሳታፊዎች ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ የሚያቀርቡት ትርዒት በዳኞች ተገምግሞ አሸናፊዎች ይለያሉ። ነገ በተመሳሳይ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትዕይንታቸውን እንዲያቀርቡ መርሐግብር ተይዞላቸዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review