2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ በተቀናጀ መልኩ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅት እየተደረገ ነው-የቅድመ ዝግጅት ኮሚቴ

You are currently viewing 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ በተቀናጀ መልኩ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅት እየተደረገ ነው-የቅድመ ዝግጅት ኮሚቴ

AMN-የካቲት 13/2017 ዓ.ም

በመጪው ሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ በስኬት ለማስተናገድ በተጀመሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ፣ በኢትዮጵያ በምግብ ራሰን ለመቻል እየተደረጉ ያሉ ተግባር ተኮር እና ለውጥ ያመጡ ሥራዎችን በተመለከተ ገለፃ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በተቀናጀ መልኩ ቀጣዩን ጉባኤ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ በርካታ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ ኮንፈረንሶችን በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን በማስታወስ፤ በቀጣይ ሐምሌ ወር ለሚካሄደው ጉባኤም ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በመጠቀም የተሟላ ዝግጅት እንደምታደርግ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልዑካን ቡድን መሪ ዶ/ር እስጢፋኖስ ፎሽው፣ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመንግሥት እየተከናወነ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች በማድነቅ ቀጣዩን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንደምታስተናግድ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በዚህ የጉባኤ ቅድመ ዝግጅት የኮሜቴ ውይይት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቋማት እና በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review