2ኛው ዙር የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ከጷግሜ 3 – ጷግሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሔዳል።
ጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መቋቋም፣ ድህነት ቅነሳና ሌሎች በዘርፉ ላሉ ማነቆዎች መፍትሄ ማፈላለግ ላይ ትኩረቱን ያደረጋል ተብሏል።
ጉባኤው በታላላቅ የሐገር ባለስልጣናት ደረጃ የሚካሔድ ሲሆን 45 የአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉባኤውን ለማካሔድ የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን አስመልክቶ የኢፌድሪ ልማትና ፕላን ሚኒስቴርና የአፍሪካ ህብረት አየር ንብረት ኮሚሽን በጋራ ለሚዲያ ባለሙያዎች መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።
በሔኖክ ዘነበ