የካቲት 13/2017 ዓ.ም
በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አሰተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ኒዕመተላህ ከበደ እና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ በአቶ ሰለሞን አማካኝነት ቀርቧል።
አቶ ሰለሞን በዚሁ ወቅት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት አንጸባራቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
በሀብታሙ ሙለታ